የአነስተኛ ንግድ ካፒታል መዳረሻ ፕሮግራም

ሃምሌ 2024 ተዘምኗል

የእኛ የአነስተኛ ንግድ ካፒታል ተደራሽነት ፕሮግራም (CAP) በአናሳ ቁጥር በሆኑ ባለቤትነት የተያዙ ንግዶች እንዲያድጉ ያግዛል። CAP የበለጠ ፍትሃዊ እኩልነት ያለው የንግድ ገጽታ በመፍጠር፣ ብድሮች እና ንግድ በገንዘብ ማቋቋምን ጨምሮ በዋጋ ተመጣጣኝ የመነሻ ገንዘብ እንዲደረስበት ቅድሚያ ይሰጣል።

ስለ ካፒታል ተደራሽነት ፕሮግራም (CAP)

የኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ከማህበረሰብ አበዳሪዎች ጋር በመተባበር የሚያሟሉ ብድሮች ክፍያን ከዋናው 20% በታች በመክፈል የመበደር ወጪውን ይቀንሳል። ይህ ብቁነትን ለሚያሟሉ፣ አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ባለቤትነት ያሉ ንግዶች ዕዳን ለመቆጣጠር እና የገንዘብ ልውውጥ ጤናቸውን ለማሻሻል ይረዳል።

ንግዶች ለ CAP ሽልማት አያመለክቱም። ብቁነት በሚከተሉት ምድቦች ላይ በእርስዎ አበዳሪ የብድር መፍቀድ ይታሰባል።

የCAP ሽልማት ምድቦች:

  • የአነስተኛ ንግድ ፍሌክስ የድጋፍ ገንዘብ 2 (Flex Fund 2) የብድር ካፒታል ሽልማት ክፍያ: ይህ ሽልማት የንግድ ባለቤቶች የስቴት አነስተኛ ንግድ ብድር ተነሳሽነት (SSBCI) Flex Fund 2 ብድሮችን የብድር ዋናውን 20% ወይም $30,000 ዶላር (ከሁለቱ ያነሰ የትኛውንም) በመሸፈን እንዲከፍሉ ይረዳል።

    • ለአነስተኛ ንግድ Flex Fund 2 ብድር የተፈቀደላቸው እና የCAP የብቃት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ንግዶች ወዲያውኑ ለ CAP ሽልማት ይታሰባሉ።

    • የንግድ ሥራ በገንዘብ ለማቋቋም እያሰቡ ከሆነ እና ለአነስተኛ ንግድ Flex Fund 2 ብድር ብቁ ከሆኑ፣ እባክዎን እነዚህን የማህበረሰብ አበዳሪዎች ያግኙዋቸው።

  • የማህበረሰብ አበዳሪ ካፒታል ክፍያ ሽልማት: ይህ ሽልማት ከመነሻ ዋናው ገንዘብ 20% ወይም $30,000 ዶላር (ከሁለቱ ያነሰ የትኛውንም) ከተሳታፊ የማህበረሰብ አበዳሪዎች ለሚመጡ ብቃት የሚያሟሉ ብድሮች ይከፍላል።

  • ባህላዊ ምላሽ ሰጪ የመነሻ ገንዘብ ክፍያ ሽልማት: ይህ ሽልማት ከመነሻ ዋናው ገንዘብ 20% ወይም $30,000 ዶላር (ከሁለቱ ያነሰ የትኛውንም) በሸሪዓ (Sharia) የሚያሟሉ እና ገቢን መሰረት ባደረጉ በገንዘብ ማቋቋሚያ ምርቶች ላይ ይከፍላል።

    • ለ CAP ብቁነት መስፈርቶች ያሟሉ አንድ ብቁ የሆነ ብድር ወይም የሸሪአ ሁኔታ ያሟላ የገንዘብ ድጋፍ የተፈቀደላቸው ንግዶች ለ CAP ሽልማት ይታሰባሉ።

    • የንግድ ሥራ በገንዘብ ለማቋቋም እያሰቡ ከሆነ እና ብቁ የሆነ የገንዘብ ማቋቋሚያ ለማግኘት ብቁ ከሆኑ፣ እባክዎን ከእነዚህ የማህበረሰብ አበዳሪዎች ጋር ይገናኙ።

    • መስከረም 2024 ውስጥ ጀምሮ ፈቃድ ለጸቀደላቸው ብድሮች/ የመቋቋሚያ ገንዘብ ምርቶች ለ CAP ሽልማት ብቁነት ይታሰባሉ።

ለ CAP ብቁ ለመሆን ንግዶች የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው:

  • ለትርፍ የተቋቋመ ንግድ፣ በነጻ የግል ባለቤትነት የተያዙ እና በሲያትል ከተማ ገደቦች ውስጥ የሚገኙ መሆን።

  • አሁን ላይ የሚሰራ/ቀኑ ያላለፈበት የሲያትል የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው መሆን።

  • ከ12 ወራት በላይ በስራ ላይ መቆየት።

  • የከተማዋ ንግድ እና ሥራ (B&O) ታክስ ያስገቡ እና ያልተከፈለ ግብር ካለ ሙሉ በሙሉ ታክስ መክፈል ወይም በምርጫ በሁለት ወራት ውስጥ ማሟላት።

  • ከ 50 የሚበልጡ የሙሉ ጊዜ አቻ (FTE) ሠራተኞች መኖር አያስፈልግም።

  • ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ከ$2 ሚሊዮን ዶላር የማይበልጥ መሆን።

  • ከስቴት እና የአካባቢ ተወካይ ድርጅቶች መስፈርቶች ጋር በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆን።

  • የዋናው መነሻ ገንዘብ የመክፈያ ሽልማት በሚሰጥበት ጊዜ በብድር ክፍያዎች ላይ ወቅታዊ መሆን።

ንግዶች ለ CAP ሽልማት ለማመልከት ብቃት የማያሟሉ መሆን:

  • ከሲያትል ከተማ ገደብ ውጭ የሚገኙ ንግዶች ወይም ከ 50% ያነሱ በሲያትል ውስጥ የሚሰሩ መሆን።

  • በሲያትል ማዘጋጃ ቤት ህግ አንቀጽ 6.270 ስር የሚተዳደሩ "የአዋቂዎች መዝናኛ" ንግዶች። 

  • የሀሺሽ/ካናቢስ ሱቆች፣ አብቃዮች እና ማከፋፈያዎች ብቁ አይሆኑም። 

  • 501(c)(3), 501(c)(6) ወይም 501(c)(19) ለትርፍ ያልተቋቋሙ አካላት። 

የCAP ሽልማት ውሎች:

  • ብቁ የሆኑ አነስተኛ ንግዶች እስከ $30,000 ዶላር ወይም 20% ዋና የመነሻ ገንዘብ ብድር መጠን (ከሁለቱ ያነሰ የትኛውም) ሊቀበሉ የሚችሉ።

  • ተሸላሚ ሽልማቱ በተሰጠበት ወቅት (ምንም በብድሮች ጥፋት የሌለበት) መሆን አለበት።

  • የሽልማት ብቁነት በአበዳሪው ይወሰናል።

  • ተሳታፊ አበዳሪዎችን እዚህ ይመልከቱ።

 

አስፈላጊ ሰነድ

በካፒታል ተደራሽነት ፕሮግራም ሽልማት ውስጥ ፍላጎት ያላቸው አነስተኛ ንግዶች ለብቻ የተለየ የማመልከቻ ቅጽ አይሞሉም። ብቁነት የሚወሰነው በተሳታፊ አበዳሪዎች ነው።

ብቁ የሆኑ አመልካቾች የሚከተሉትን ሰነዶች በቅደም ተከተል ለእያንዳንዳቸው አበዳሪ ማቅረብ ያቀርባሉ:

  • የተዋሃደ የንግድ መታወቂያ (UBI) ቁጥር (ዘጠኝ አሃዞች)።

    • ለዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፈቃድ ሲያመለክቱ ንግዶች አንድ ወጥ የሆነ የንግድ መለያ መታወቂያ (UBI) ቁጥር ያገኛሉ። ይህ በገቢዎች መምሪያ በመስመር ላይ ወይም በፖስታ መላላኪያ በኩል ሊደረግ ይችላል። አመልካቾች የተዋሃደ የንግድ መለያ ቁጥራቸውን በመስመር ላይ መፈለግ ይችላሉ።

  • የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (ስድስት አሃዞች)።

    • በሲያትል ውስጥ የንግድ ሥራ የሚሠራ ማንኛውም ሰው የሲያትል የንግድ ፈቃድ ግብር፣ እንዲሁም የከተማ የንግድ ፈቃድ ቁጥር፣ የከተማ ደንበኛ ቁጥር ወይም አጠቃላይ የንግድ ፈቃድ በመባል የሚታወቅ የምስክር ወረቀት ሊኖረው ይገባል። የንግድ ባለቤቶች ይህንን የምስክር ወረቀት በየዓመቱ እስከ ታህሳስ 31 ድረስ ማደስ አለባቸው።

    • ይህ የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር ከዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፈቃድ የተለየ ነው። የንግድ ድርጅቶች የነሱን ቁጥራቸውን በከተማ ንግድ ፍቃድ የንግድ መፈለጊያ መሳሪያ ማግኘት ካልቻሉ፣ የዋሽንግተን ግዛት ፈቃድ ብቻ ሊኖራቸው ይችላል።

    • ንግዶች ለከተማ ንግድ ፈቃድ ማመልከት እና በመስመር ላይ ወይም በፖስታ መላላክ ማደስ ይችላሉ።

  • የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብሮች።

    • ምንም ዓይነት የሥራ እንቅስቃሴ ባይኖር ወይም ምንም ዓይነት የግብር ዕዳ ባይኖርበትም እያንዳንዱ ንግድ ለከተማው ፋይል እና ሪፖርት ማድረግ አለበት። የሲያትል የንግድ ግብር ከዋሽንግተን ስቴት የንግድ ግብር ጋር ተመሳሳይ አይደለም፤ የንግድ ድርጅቶች የሲያትል ታክስን ከስቴቱ ግብሮች ለይተው ለየብቻ ፋይል ማድረግ አለባቸው።

    • ዓመታዊ ግብር የሚከፈልበት ጠቅላላ ገቢ ከ $100,000 ዶላር በታች ከሆነ ንግዶች አጠቃላይ የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብር አይኖራቸውም፣ ነገር ግን ንግዶች አሁንም ፋይል ማድረግ አለባቸው።

    • ንግዶች በመስመር ላይ ወይም በፖስታ መላላክ ፋይል ማድረግ እና ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ስለእነዚህ ግብሮች ተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ንግዶች ወደ ሲያትል ፋይናንስ በ Tax@seattle.gov መድረስ ይችላሉ።

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

ለአነስተኛ ንግድ Flex Fund 2 ብድር ወይም ሌላ ለመክፈል የሚመች የገንዘብ ነክ ምርት ብቁነት ምን መጠቀም እችላለሁ?

የአነስተኛ ንግድ Flex Fund 2 ብድሮች እና ሌሎች የገንዘብ ነክ ምርቶች እስከ ሙሉ የንግድ ስራ ማስኬጃ ፍላጎቶች እንደ ደመወዝ ክፍያ፣ ኪራይ፣ መገልገያዎች፣ አቅርቦቶች እና ሌሎች የዕለት ተዕለት ወጪዎች ያሉትን መጠቀም ይችላሉ። የሆነ ሆኖ፣ እባክዎን ለተለየ የብድር የድጋፍ ገንዘብ አጠቃቀም እንደ ቅደም ተከተላቸው የእርስዎን አበዳሪ ያነጋግሩ።

እንዲሁም የአነስተኛ ንግድ Flex Fund 2 በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን እዚህ ደግሞ መገምገም ይችላሉ።

የ CAP ብድር ለመነሻ የስራ ገንዘብ ክፍያ እንዴት ነው የሚሸለመው?

ብቁ የሆኑ ንግዶች የCAP ሽልማቶችን በሁለት ክፊያዎች ይቀበላሉ: የ12ኛ እና የ24ኛ ወርሃዊ ክፍያዎችን እንደ አጠናቅቁ። 

ተሳታፊ የማህበረሰብ ልማት የገንዘብ ነክ ተቋማት እነማን ናቸው?

የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት ለንግድ የመነሻ ገንዘብ ተደራሽነት ፕሮግራም ከተለያዩ የአካባቢ የማህበረሰብ ልማት የገንዘብ ነክ ተቋማት ጋር በመተባበር እየሰራ ነው። እባክዎ በእያንዳንዱ የሽልማት ምድብ ውስጥ የተሳተፉ አበዳሪዎችን ዝርዝር ይከልሱ።

ለብድር ብቁነት ካላሟላሁ ምን ይሆናል?

ከላይ የተዘረዘሩትን የብቃት መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች በሙሉ እንዲያመለክቱ እናበረታታለን። ከሌሎች ባንኮች እና ከተለመዱ አበዳሪዎች ጋር ሲነጻጸር፣ የማህበረሰብ አበዳሪዎች የብድር ጥያቄዎችን ሲገመግሙ የበለጠ ተለዋዋጭነት አላቸው።

አሁንም፣ አንድ አነስተኛ ንግድ ለብድር ወይም ለሌላ የገንዘብ ነክ ምርት ብቁ የማይሆንባቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ። የእርስዎ አነስተኛ ንግድ ብቃት የሚያሟላ ካልሆነ፣ ከከተማው ለሌሎች የመቋቋሚያ ገንዘብ ማግኛ አማራጮች ብቁ መሆንዎን ለማረጋገጥ ከ CAP የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪዎች ጋር እንዲገናኙ ይደረጋሉ።

ተጨማሪ መረጃ 

ስለ ፕሮግራሙ አጠቃላይ ጥያቄዎች፣ እባክዎን የCapital Access and Finance አማካሪ፣ አግራጅ ዳንጋል (Agraj Dangal) ን፣ በ agraj.dangal@seattle.gov ያግኙ ወይም በ (206) 665-1012 ይደውሉ።

CAP ከአነስተኛ ቁጥር ወገን-ባለቤትነት ያላቸውን ንግዶች በሚከተሉት በኩል ያበረታታል፡

  1. ፍትሃዊ እኩልነት ተደራሽነት

    • CAP ከባህላዊ የድጋፍ ገንዘብ ምንጮች ሥርዓታዊ በሆነ ስልት ለተገለሉ ሰዎች በዋጋ ተመጣጣኝ የመቋቋሚያ ገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ ያረጋግጣል።

  2. ክፍተቱን መዝጋት

    • CAP ስኬታማ እንዲሆኑ እድል እየሰጣቸው፣ ከተገቢው በታች ሲገለገሉ የቆዩትን አነስተኛ ንግዶች የገንዘብ እድሎችን ያቀርባል።

  3. የማህበረሰብ ሀብት ግንባታ

    • CAP ለሁሉም ለበለጠ ብልጽግና ንጣፍ መንገድን በመክፈት እና ፍትሃዊ እኩልነት ሲያትል ለሁሉም በማድረግ፣ የንግድ እድገትን እና ዘላቂነትን ይደግፋል።

በእኛ የመጀመሪያ ዙር የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ CAP የዋሽንግተን ስቴት የአነስተኛ ንግድ Flex Fund ብድሮችን 25% የብድሩን ዋና ገንዘብ በመክፈል ወጭውን ቀንሷል። በሃምሌ 2021 እና በግንቦት 2023 መካከል፣ CAP $6.9 ሚሊዮን ዶላር ለ295 የሲያትል ንግዶች አከፋፈለ። ይህ በእኛ አከባቢ ኢኮኖሚ ውስጥ $27.8 ሚሊዮን ዶላር ዝቅተኛ ወለድ ያለው የFlex

Economic Development

Markham McIntyre, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 5752, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 94708, Seattle, WA, 98124-4708
Phone: (206) 684-8090
Phone Alt: (206) 684-0379
Fax: (206) 684-0379
oed@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Economic Development

The mission of the Office of Economic Development (OED) is to help create healthy businesses, thriving neighborhoods, and community organizations to contribute to a robust economy that will benefit all Seattle residents and future generations.