በ COVID-19 ለተጎዱ አነስተኛ ንግድ አሠሪዎች ወደ ሥራ መመለስ መረጃ

የሥራ ደህንነት መምሪያ (.ኤስ..) አሠሪዎችና ሠራተኞቻቸው COVID-19 ወረርሽኝ ማገገሚያ ወቅት ወደ ሥራው መመለሳቸውን ሲጀምሩ ለመርዳት የተዘጋጀ መረጃ አለዉ። ለኤ.ኤስ. መረጃ ዋና አገናኝ  https://esd.wa.gov/newsroom/covid-19 (እንግሊዝኛ ብቻ) ነው። ይህ መረጃ በየግዜዉ ስለሚሻሻል ብዙ ጊዜ ተመላልሰው ይመልከቱ።

የቀጣሪ መረጃ

የአሰሪ ጥያቄዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዓይነት፣ በአሰሪው ድህረ ገጽ ላይ ይመለሳሉ፡ https://esd.wa.gov/newsroom/covid-19-employer-information

  1. ወደ ስራ ለመመለስ ፈቃደኛ ላልሆነ ሠራተኛ ወደ ሥራ እንድመለስ ዕድል ሰጥቻለሁ። ምን ማድረግ ነው የሚገባኝ?

ግለሰቦች በአጠቃላይ የሥራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞችን በመቀበልና ወይም ከአሠሪዎቻቸው ተስማሚ ሥራ ወደ ሆነው የመመለስ መካከል አማራጭ የላቸውም። ግለሰቦች በፌዴራል CARES ሕግ መሠረት የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን ወይም የወረርሽኝ ሥራ አጥነት ድጋፍ መቀበል ለመቀጠል ተስማሚ ስራን ላለመቀበል ጥሩ ምክንያት ሊኖራቸው ይገባል።

አንድ ሠራተኛ ሥራውን ውድቅ ሊያደርገው እና ሥራ አጥነትን መሰብሰቡን ለመቀጠል ጥሩ ምክንያቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡

  • በ COVID-19 የታመመ ወይም በ COVID-19 የታመመውን የቤተሰብ አባልን መንከባከብ።
  • ትምህርት ቤታቸው ወይም የህፃናት መንከባከቢያቸው ስለተዘጋ ልጅ ለመንከባከብ ቤት መቆየት ካስፈለገ።
  • ተመልሰው የሚመጡበት መደብ በከፍተኛ ሁኔታ ከተቀየረ፣ ደሞዝ ደመወዛቸውን በእጅጉ ከተቀነሰ፣ ወይም የሥራ ቦታው በጣም ርቆ ወደሚገኝ ቦታ ከተዛወረ።

አንድ ሰራተኛ አዲስ ወይም የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅምን እንደገና በከፈተ ጊዜ እርስዎ እንዲያውቁት ይደረጋል እና የሰራተኛውን በእራሳቸው ስህተት ያለመቀነሳቸዉ አቤቶታን መከራከር ይችላሉ። የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን ለሠራተኛ ለማቅረብ በስራ ደህንነት ክፍል (ዲፓርትመንቱ) የመስጠት ዉሳኔን ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ።
 

  1. ወደ ሥራው ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆነ እና ሥራ አጥነትን መሰብሰቡን የቀጠለውን ሰዉ እንዴት ሪፖርት አደርጋለሁ?

ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ወደ ሥራ የመመለስ ዕድል መቀበል አለመቀበሉን በትክክል ማረጋገጥ አለበት። ወደ ሥራ የመመለስ ዕድል እንደደረሳቸው ለኢ.ኤስ.ዲ ሲያሳውቁ የቀጣይ ሥራ አጥነትን ብቁነት ለመወሰን እዉነታ የመፈለግ አካል እናነጋግራቸዋለን። እንደ ቀጣሪ በረስዎ ተነሳሽነት በ  eServices  አካዉንት በኩል የስራ እምቢታ ጉዳዮችን ሪፖርት በማድረግ ይችላሉ ወይንም መረጃውን ወደ የይገባኛል ጥያቄ ማእከል በመላክ ለ ESD ማሳወቅ ይችላሉ።
 

  1. ለስራ ብቁ ወይም ለሥራ መገኘት አለመቻላቸውን ለሥራ መመለስ ዕድል አለመቀበላቸዉን፣ ወይም ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ ገቢ መቀበላቸዉን እውነተኛ ሪፖርት የማያደርጉ ግለሰቦች የሚደርስባቸዉ መዘዝ ምንድን ናቸዉ?

ለስራ ብቁ ወይም ለሥራ መገኘት አለመቻላቸውን፣ የሥራ ዕድል እንደተሰጣቸዉ፣ እና ማንኛዉንም ገቢ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ሲያቀርቡ ግለሰቦች በትክክል ሪፖርት ማድረግ አለባቸው። ትክክለኛ ሥራን እና ገቢዎችን ሪፖርት ሳያሳውቁ ወይም ለምን ከሥራ እንደተለዩ ሆን ብለው ሪፖርት አለማድረግ ዓይነት የደንቦች ጥሰት ጥቅማ ጥቅሞችን መከልከል እንዲሁም ትርፍ ክፍያ እና ኢኤስዲ የሚሰበስባቸው ቅጣቶችን ያስከትላል። እንደነዚህ ያሉ እርምጃዎች የወንጀል ክስ እንኳን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ማጭበርበር ማለት ስለ አንድ የይገባኛል ጥያቄ መረጃ እያወቁ መደበቅ ማለት ነዉ። የሥራ አቅርቦትን የማይቀበሉ እና በሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎቻቸው ላይ የሥራ ዕድሉን እንዳልተቀበሉ ሪፖርት የማያደርጉ ግለሰቦች ጥቅማጥቅሞችን ሊከለከሉ ና ለማጭበርበራቸዉ ተጨማሪ ቅጣትን ሊያገኙ ይችላሉ። 

  1. ጊዜያዊ ቀነሳ እና ዉስን ቀነሳ (furlough) መካከል ልዩነት አለ?
    • ጊዜያዊ ቅነሳዎች አሠሪዎች በሥራ መቀነስ ምክንያት ሠራተኞቻቸውን እንዲለቁ ሲያደርጉ ማለት ነው። አሠሪዎች እነዚያን ሠራተኞች መልሶ መቅጠር የለባቸውም።  
    • ዉስን ቅነሳዎች ( Furloughs ) ለተወሰነ ጊዜያት ሙሉ በሙሉ ከሥራ ማቆም ወይም የስራ ሰዓትን የሚቀንሱ ጊዜያዊ ቅነሳ ዓይነቶች ናቸው። ለምሳሌ ፣ ለአንድ ዓመት በሳምንት አንድ ቀን መቀነስ።
  2. የእኔ ጥቅማ ጥቅሞች ክፍያዎች በተመለከተስ?

በአዲሱ የአደጋ ጊዜ ህጎች በንግድ ቦታዎች ውስጥ ክዋኔዎችን ለመዝጋት ወይም ለመቀነስ የሞዳርጉ ከ COVID-19 ኢንፌክሽን ጋር የሚዛመዱ ጊዜያዊ መዝጋቶች እንደ ልዩ ሁኔታዎች ይቆጠራሉ። የጥቅማጥቅም ክፍያዎችን እፎይታ መጠየቅ ይችላሉ። ሠራተኞች እርስዎ የሚጸጧቸዉን ከቤት ሆነዉ የመሥራት ዕድልን መቀበል አለባቸው።

  1. ለንግድ ድርጅቶች የገንዘብ ቅጣቶችስ?

በ ”COVID-19” ምክንያት የግብር ሪፖርቶችን ዘግይተው ላስገቡ ፣ ዘግይተው ግብር ለከፈሉ አሊያም በወቅቱ ለሚጠየቁት መረጃ ምላሽ ላልሰጡ አሠሪዎች የገንዘብ ቅጣቶች ሊተዉ ይችላሉ። ማንኛውንም ተጨማሪ እርዳታ ከፈለጉ ሊንዳ ሄለንበርግ በ 206.628.6988 ይደዉሉ በ Lhelenberg@seattlejobsinit.com ኢሜል ይላኩ።

ለአነስተኛ የንግድ ሥራ አሠሪዎች ተጨማሪ የድጋፍ ምንጮች

የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በ  COVID-19 ወረርሽኝ የተጎዱትን ሠራተኞች እና አነስተኛ የንግድ ሥራዎችን የተጎዱ ድርጅቶችን ለመርዳት ከክልላችን ፣ ከስቴታችን እና ከፌዴራል አጋሮቻችን ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።

ለአጠቃላይ ጥያቄዎች እባክዎን ወደ OED@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ ወይም 206-684-8090 ይደውሉ።

ሲደውሉ ቀጥታ ሰው ወይም የድምፅ መልእክት ሊያገኙ ይችላሉ። የድምፅ መልዕክቱን ካገኙ እባክዎን ይንገሩን፡

  • የርስዎ ስም
  • ስልክ ቁጥር
  • በእንግሊዝኛ የሚፈልጉትን ቋንቋ
  • ምን ድጋፍ ያስፈልግዎታል

ከሲያትል ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ለአነስተኛ ንግዶች የድጋፍ ምንጭ ዝርዝር

የ 2ኛ ዙር እንደገና መክፈት መሳሪያዎች

ጊዜያዊ የቤት ውጭ ካፌ ፣ የሸቀጣሸቀጦች ማሳያ እና የሽያጭ ፈቃዶች

ለPPP እና ለEIDL ብድሮች ነፃ የ SBA ቴክኒካዊ ድጋፍ

Economic Development

Markham McIntyre, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 5752, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 94708, Seattle, WA, 98124-4708
Phone: (206) 684-8090
Phone Alt: (206) 684-0379
Fax: (206) 684-0379
oed@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Economic Development

The mission of the Office of Economic Development (OED) is to help create healthy businesses, thriving neighborhoods, and community organizations to contribute to a robust economy that will benefit all Seattle residents and future generations.