የሲያትል የማመላለሻ እቅድ
አማርኛ • اَلْعَرَبِيَّةُ • 繁体字 • Français • हिन्दी• 日本語 • ភាសាខ្មែរ • 한국어 • ລາວ • Oromiffa • русский язык • af-Soomaali • Español • Tagalog • ภาษาไทย • ትግርኛ • Tiếng việt • украї́нська мо́ва • English
የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ በሚቀጥሉት 20 አመታት በከተማችን መዘዋወር ምን እንደሚመስል ሃሳባዊ ቅኝት ያደርጋል። በሲያትል ውስጥ ላሉ እያንዳንዱ ሰዎች ሁሉ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የበለጠ ፍትሃዊ እኩልነት፣ አስተማማኝ፣ ዘላቂ እና በዋጋ ተመጣጣኝ የጉዞ አማራጮችን የሚያመጡ ብልህ መዋዕለ ንዋዮችን ለማድረግ ዓላማ እናደርጋለን። የሲያትል ከተማ ምክር ቤት ሚያዝያ 23 ቀን 2024 የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ በሙሉ ድምፅ እንዲፀድቅ ወስኗል።
አንድ እቅድ አንድ ራዕይ
ቀደም ባሉት ጊዜያት፣ በእግር ለመሄድ እና ለማንከባለል፣ ብስክሌት ለመንዳት፣ ለሕዝብ መጓጓዣ እና ጭነት የተለያዩ እቅዶች ነበሩን። እነዚህ የአሰራር ስልታዊ ዘዴ እቅዶች ተብለው ይጠሩ ነበር። አሁን፣ የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ (STP) እነዚህን ሁሉ ዕቅዶች ወደ አንድ ትልቅ ራዕይ ያመጣል።
ከአንድ የሲያትል አጠቃላይ እቅድ ጋር የ STPን እጅ ለእጅ ተያይዘን አዳብረናል። አንድ የሲያትል እቅዱ ከተማችን እንዴት በመኖሪያ ቤት፣ በስራዎች፣ እና በመዋዕለ ንዋይ እንደምታድግ በሚቀጥሉት 20 አመታት ወቅት ይመራል። መጓጓዣ ደግሞ የዚህ እቅድ ዋና አካል ነው።
የሚከተሉትን ነገሮች ለማድረግ የሲያትል የመጓጓዣ እቅድን እንጠቀማለን።
- ወደፊት መጓጓዣን የቱ ላይ ማሻሻል እንዳለብን ለይተን እናውቃለን።
- ፕሮግራሞቻችንን እና ፕሮጀክቶቻችንን ከመጓጓዣ እቅዳችን ጋር እናጣጥማለን እና እድገታችንን እንከታተላለን።
- ለወደፊቱ የመጓጓዣ ፍላጎቶችን እንዴት እንደምንከፍል እናቅዳለን።
እቅዱ እንዴት ነው የተዘጋጀ?
እኛ ከእኛ ጋር የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ለመፍጠር እንዲረዱን ጠይቀንዎታል። በሺዎች የምትቆጠሩ እናንተ ሃሳቦቻችሁን አካፍላችሁ እና ግብአታችሁን መስጠታችሁ እቅዱን በቀጥታ ቀርጾታል። እንዴት በሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ላይ አብረን እንደሰራን የበለጠ ይረዱ:
የSTP ረቂቁን ለማዘጋጀት ወደ ሁለት ዓመታት በሚጠጋ ማህበረሰብ የመድረስ ተሳትፎ፣ በመንግስት እቅድ ማድረግ ውስጥ ብዙ ጊዜ የተገለሉ ግለሰቦችን ድምጽ በማጉላት ላይ አተኩረን ነበር። ይህ ጥቁር፣ ተወላጆች፣ ወይም የቀለም ማህበረሰብ አካል የሆኑትን እንደ LGBTQIA+ ተለይተው የሚታወቁ ግለሰቦች፤ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች፤ አዲስ ሠፋሪ ማህበረሰቦች እና እንግሊዝኛ ተናጋሪ ያልሆኑ፤ ወጣቶች፤ አረጋውያን አዋቂዎች፤ እና አካል ጉዳተኝነት ያላቸው ሰዎችን ያጠቃልላል።
ያደረግነው ይሄው:-
- እንደ የአካባቢ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮች፣ ቤተመጻሕፍት፣ የገበሬ ገበያዎች፣ የማህበረሰብ ስብሰባዎች፣ በዓል አከባበሮች፣ እና ቀደም ሲል አገልግሎት የተነፈጉ ሰፈሮች ባሉ በተለያዩ አካባቢዎች በሚደረጉ የማዳረስ ዝግጅቶች በኩል በሺዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ግንኙነት አድርገናል።
- የተሳትፎ ሂደታችንን ለማስፋፋት እና ወደፊት ለማስኬድ ከጎረቤቶች ማህበረሰብ አገናኞች መምሪያ (CLs) ጋር ትብብር አድርገናል።
- ማህበረሰብ-መሠረት ካደረጉ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት መስርተናል እና እንደ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎችን፣ ስብሰባዎችን፣ ዝግጅቶችን፣ ክስተቶችን፣ የመስክ ጉዞዎችን፣ እና የአንድ ለአንድ ቃለ-መጠይቆችን ጨምሮ የተሳትፎ ጥረቶቻቸውን ደግፈናል።
- ሲያትል ዙሪያ አቋራጩን የግቢ ምልክቶችን፣ ሰፋፊ የሚለጠፉን እና የጽሑፍ ማስታወቂያዎችን አሰራጭተናል።
- ተለዋዋጭ በሆነ የሲያትል መጓጓዣ እቅድ እንቅስቃሴ በመስመር ላይ የተሳትፎ ማእከል ላይ የተሳትፎ እድሎችን እና ዝመናዎችን በመጋራት ለማህበረሰቡ መረጃ በመስጠት እንዲቆዩ አድርገናል።
- እና ተጨማሪም ብዙ።
የተማርነው ይሄው:-
ደረጃ 1 -
ደረጃ 1 ለወደፊቱ የሲያትል የመጓጓዣ ስርዓት እንድናዳብር የረዳን የጋራ ራዕያችን፣ በእርስዎ የመጓጓዣ ፍላጎቶች እና ቅድሚያዎች ላይ ያተኮረ ነው። የኛ ደረጃ 1 የተሳትፎ ዘገባ ከግንቦት እስከ ነሐሴ 2022 ድረስ ያለውን ተሳትፎ በዝርዝር ያብራራል እና ከሲያትል ማህበረሰቦች ጋር እቅዱን አብረን በጋራ ለመፍጠር የሚወሰዱትን ዋና ዋና ቁልፍ መንገዶችን ይዘረዝራል።
ደረጃ 2 -
በደረጃ 2 ወቅት፣ በደረጃ 1 ጊዜ ከእናንተ የሰማነውን አካፍለናል እና የእርስዎ ግብአት እንዴት የእቅዱን ራዕይ፣ ግቦች እና አላማዎች እንደሚመራ አሳይተናል። እንዲሁም ወደፊት እንዴት መዘዋወር እንደሚፈልጉ፣ እኛ ምን አይነት እርምጃዎች እንድንወስድ እርስዎ እንደሚፈልጉ እና በእኛ ረቂቅ የመጓጓዣ ካርታዎች ላይ ደግሞ ምን ማየት እንደሚፈልጉ እንዲያካፍሉ ጠይቀንዎታል።
የኛ ደረጃ 2 የተሳትፎ ማጠቃለያ ዘገባ ከመስከረም 2022 እስከ የካቲት 2023 ድረስ የነበረውን ተሳትፎ በዝርዝር ይተነትናል። የእርስዎ ግብአት የሲያትል መጓጓዣ መምሪያ (STP) ረቂቅን እድገት ለመምራት እና የረቂቁ አውታረ መረብ ካርታዎችን ለማጣራት ጥቅም ላይ ውሏል።
ደረጃ 3 -
በ2023 በልግ ወቅት ውስጥ፣ በሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ረቂቅ ላይ የህዝብ ግብረ መልስ ጠይቀናል።
ይህም ከተማ አቀፍ የመስመር ላይ ተሳትፎን፣ በአካል በመገኘት ዝግጅቶችን መከታተል፣ እና ከጎረቤት ማህበረሰብ ግንኙነት መምሪያ ጋር በመተባበር ለመሥራት ለሚከተሉት ማህበረሰቦች ትኩረት መስጠትን ለማካሄድ ያካትታል: ጥቁር፣ ተወላጆች እና ሌሎች የቀለም ሰዎች (BIPOC)፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው፣ አዲስ ሰፋሪ እና ስደተኛ፣ በዕድሜ እየገፉ የመጡ አዋቂዎች፣ ሴቶች፣ የቤት ወይም በመኖሪያ ቤት እጦት ድህንነት አጥ ልምድ የሚያጋጥማቸው ሰዎች፣ እና በአካል ጉዳተኛነት የሚኖሩ ሰዎች።
ለበለጠ መረጃ: ደረጃ 3 የተሳትፎ ማጠቃለያን ይመልከቱ
ግቦቻችን
STP ስድስት ግቦች አሉት። እያንዳንዱ ግብ ግቦቻችንን ለማሳካት ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ስልቶች እና ድርጊቶች አሉት።
ደህንነት
ከደህንነት ጋር መምራት
እኛ ሲያትል ውስጥ ለተጓዦች ደህንነት ቅድሚያ እንሰጣለን። ግባችን ምንም አይነት ከባድ ጉዳት ወይም ገዳይ የግጭት አደጋዎች እንዳይኖር ነው። ቁልፍ እርምጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
- መንገዶቻችን ደህንነታቸው የተሻለ የተጠበቀ እንዲሆን የተሽከርካሪ ፍጥነትን እንቀንሳለን።
- ከባድ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወይም መከሰታቸው የማይቀር ዓይነት ከሆነ የደህንነት መዋዕለ ንዋይ ላይ እናተኩራለን።
እኩልነት
የመጓጓዣ ፍትህ ማዕከላዊ ነው
ከመጓጓዣ ጋር የተዛመዱ ኢፍትሃዊ እኩልነትን ለመፍታት ከማህበረሰቡ ጋር እንሰራለን። ቁልፍ እርምጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
- እቅድ በማውጣት እና በውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ የቀለም ማህበረሰቦችን እና ከተገቢው በታች የተወከሉ ቡድኖችን ድምጽ ማዕከል እናደርጋለን።
- ለተጎዱ ማህበረሰቦች ቅድሚያ በመስጠት ኢፍትሃዊ እኩልነትን እንፈታለን።
ዘላቂነት
የአየር ንብረት እርምጃ (Climate Action)
ለአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራ እና በአየር ንብረት ፍትህ መሰረት ምላሽ እንሰጣለን። ቁልፍ እርምጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
- ንፁህ፣ ዘላቂ የጉዞ አማራጮችን በማስተዋወቅ የአከባቢ የአየር ጥራትን እና ጤናን እናሻሽላለን።
- ተለዋዋጭ የሆነውን የአየር ንብረት በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር የከተማ መንገዶችን በመሬት አቀማመጥና በዛፎች አረንጓዴ እናደርጋለን።
ተንቀሳቃሽነት እና ኢኮኖሚያዊ ወሳኝነት
ሰዎችን እና ሸቀጣ ሸቀጦችን ማገናኘት
ሰዎች እና ሸቀጣ ሸቀጦች ወደ ተፈለጉበት ቦታ እንዲደርሱ ለማገዝ አስተማማኝ እና በዋጋ ተመጣጣኝ የጉዞ አማራጮችን እናቀርባለን። ቁልፍ እርምጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
- እንከን የለሽ የጉዞ ግንኙነቶችን እንፈጥራለን።
- በእግር መሄድን፣ በብስክሌት መጋለብ እና ማንከባለልን የበለጠ ምቹ፣ እና በተለይም ለአጫጭር ጉዞዎች፣ ደስ የሚያሰኙ እናደርጋለን።
መኖር የሚያስችል
ለሰዎች መንገዶች፣ እኛ የምንወዳቸው ቦታዎች
የከተማ መንገዶችን ጊዜ ለማሳለፍ እና ለመጫወት የሚጋብዙ ቦታዎች አድርገን ሃሳባችን ውስጥ እናጤናለን። ቁልፍ እርምጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
- እኛ የጎዳና ላይ ቦታን እንደገና በማደላደል እና እንዲሁም ለሰዎች ቅድሚያ በመስጠት የሸቀጦችን አቅርቦት እና ተንቀሳቃሽነትን የሚያመቻቹ አስደሳች ቦታዎችን እንፈጥራለን።
- የእንኳን ደህና መጣችሁ ማህበረሰብ እና የተንቀሳቃሽነት ማዕከልን እንፈጥራለን።
ጥገና/ በጥሩ ሁኔታ የማቆየት እና ዘመናዊነት
ዛሬ እና ወደፊትም፣ የሚሰሩ መንገዶች
የከተማ መጓጓዣ መሠረተ ልማትን አሻሽለን እና ለወደፊት አዘጋጅተን እናስቀምጣለን። ቁልፍ እርምጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
- እኛ የታቀዱ የደህንነት ጥበቃ እና የአውታረ መረብ ማሻሻያዎችን በማጣመር የመንገዶቻችንን፣ የእግረኛ መንገዶችን እና ድልድዮችን ጥገና እንጠብቃለን።
- እኛ በመንገዶች፣ በእግረኛ መንገዶች፣ በህዝባዊ ቦታዎች እና በድልድዮች ጥራት ውስጥ ያለውን የአጎራባች ልዩነቶችን እንቀንሳለን።
የዕቅድ ክፍሎች
STP ለተለያዩ የመጓጓዣ ስርዓታችን ልዩ ልዩ ክፍሎች የሚያቅዱ ስምንት ተጨማሪ ምዕራፎችን፣ ወይም አካላትን/ ባህሪያትን ያካትታል። የመጓጓዣ ስርዓታችን በአንድ ላይ እንዲሠራ ለማድረግ የ STP ግብ አካል የሆነው፣ ስምንቱ አካላት በመንገዶቻችን አጠቃቀም ዙሪያ የሕዝብ መጓጓዣን፣ ብስክሌቶችን፣ እግረኞችን፣ እና ጭነትን፣ የህዝብ መንገዶችን እና የህዝብ ቦታዎችን ጨምሮ ተሸከርካሪዎች፣ ኩርባው፣ እና አዲስ እና ብቅ ባይ ተንቀሳቃሽነት ያላቸው አማራጮችን በተለያዩ መንገዶች እንዴት እንደምናቅድ እና እንደምናስተባብር የሚታዩበትን ዝርዝር ያቀርባል።
ጥረታችንን በእያንዳንዱ ባህሪ/ አካል ላይ ለማተኮር እንዴት እንደምናቅድ እነሆ:-
የሕዝብ መጓጓዣ አካል
ሰዎች መኪና ሳይኖራቸው ወደሚፈልጉት ቦታ እንዲደርሱ ሀይል ልንሰጣቸው እንፈልጋለን። የሕዝብ መጓጓዣ ዝቅተኛ ወጪ እና ዘላቂነት ያለው የጉዞ አማራጭ ነው።
ለሕዝብ መጓጓዣ አካል/ ባህሪ የእኛ ግቦች:-
- በሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT) ተደጋጋሚ የሕዝብ መጓጓዣ አውታረ መረብ አገልግሎት ደረጃዎች ለማቅረብ ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ጋር አብሮ መስራት።
- በየቀኑ፣ ቀኑን ሙሉ የሚሰራ አስተማማኝ የአውቶቡስ መስመሮች አውታረ መረብን በመገንባት ላይ ማተኮር።
- የማህበረሰብ እና የተንቀሳቃሽነት ማዕከሎችን መፍጠር እና ማሻሻል።
- የአሁኑን እና የወደፊት የቀላል ባቡር ጣቢያዎችን የተሻለ ተደራሽነት ማቀድ።
- በአጎራባቾች እና መድረሻዎች መካከል የምስራቅ-ምዕራብ ጉዞን ማሻሻል።
የጭነት እና የከተማ ሸቀጣ ሸቀጦች አካል/ ባህሪ
በአካባቢው ሰፈሮች እና ንግዶች ላይ የሚደርሰውን ተፅእኖ መቆጣጠር እያረጋገጥን እያለን፣ የአካባቢውን ኢኮኖሚ በአስተማማኝ እና ደህንነቱ በተጠበቀ የጭነት እንቅስቃሴ መደገፍ እንፈልጋለን።
የእኛ ለጭነት እና ለከተማ ሸቀጣ ሸቀጦች አካል/ ባህሪ ያሉን ግቦቻችን:
- በማምረቻ እና በኢንዱስትሪ ማዕከላት (MICs) ውስጥ የተሻለ የመጓጓዣ መሠረተ ልማት ለማቀድ እና ለመገንባት ከጭነት እና የባቡር አጋሮች ጋር መስራት።
- በምስራቅ-ምዕራብ መስመሮች ላይ በማተኮር፣ ሰዎች እና ሸቀጣ ሸቀጦች በቀላሉ ወደ ቁልፍ መድረሻዎች መሄድ መቻላቸውን ማረጋገጥ።
- ልዩ የጭነት እና የአውቶቡስ መስመሮች አጠቃቀምን ማሰስ።
- እንደ ተጨማሪ ረፋድ-ምሽት የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎቶች እና ሌሊቱን ሁሉ ጥሩ ሆኖ የሚበራ መብራት ያለው መኪና ማቆሚያ በመጠቀም፣ በሠራተኛ አቀጣጠር ማዕከላት እና MICs ለጥቁር፣ ተወላጆች፣ እና ሌሎች የቀለም ሰዎች (MICs for BIPOC)፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና ለተፈናቀሉ ሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ መዳረሻን መደገፍ።
- አሽከርካሪዎች የመኪና ማቆሚያ ፍለጋ የሚያጠፉትን ጊዜ ለመቀነስ ለንግድ ተሽከርካሪዎች ተጨማሪ የመጫኛ ቀጠናዎችን መጨመር።
የብስክሌት እና ኢ-ተንቀሳቃሽነት አካል/ ባህሪ
እንደ ኢ-የቀላል ሞተር ብስክሌት ያሉ ሁሉም ሰው ብስክሌቶችን እና በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ መሳሪያዎችን እንደ የእለት ተእለት ህይወት አካል የሚጋለብበትን ሲያትል በሃሳብ እንቃኛለን።
ለብስክሌት እና ኢ-ተንቀሳቃሽነት አካል/ ባህሪ ያሉን ግቦች:-
- እድሜያቸው እና ችሎታቸው ምንም ይሁን ምን የእያንዳንዱን ሰው ፍላጎት ለማሟላት፣ የቢስክሌት አውታረ መረብ ማስፋፋት።
- እያንዳንዱ የሕዝብ ትምህርት ቤት ደህንነቱ የተጠበቀ የብስክሌት መንገድ እንዳለው ማረጋገጥ።
- በእግር የሚሄዱ፣ ብስክሌት የሚጋልቡ፣ እና የተንቀሳቃሽነት መሳሪያዎችን የሚጠቀሙ ተጋላጭ የማህበረሰብ አባላትን ማገዝ።
- የሚሠራ ንቁ መጓጓዣን ለማስተዋወቅ በጥቁር፣ ተወላጆች፣ የቀለም ሰዎች (BIPOC) የሚመሩ ድርጅቶችን መደገፍ።
- በማህበረሰብ እና የተንቀሳቃሽነት ማእከላት ላይ በማተኮር ለብስክሌቶች፣ ባለ ቀላል ሞተር ብስክሌቶች እና ኢ-ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች ከተማ አቀፍ የመኪና ማቆሚያ ፕሮግራም መፍጠር።
- እንደ የጭነት ብስክሌቶች፣ ኢ-ባለ ቀላል ሞተር ብስክሌቶች እና አነስተኛ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላሉ አዳዲስ የተንቀሳቃሽነት መሳሪያዎች መንገዶችን ማመቻቸት።
የእግረኛ ባህሪ
በእግር መሄድ የሚያስችል ከተማ ጤናን፣ የማህበረሰብ አካል መሆን ስሜትን፣ አካባቢያችንን እና የአካባቢያችንን ኢኮኖሚ ማሻሻል ይችላል።
ለእግረኛ አካል/ ባህሪ የእኛ ግቦች:-
- የእግረኛ መንገዶችን፣ በእግር መሄጃ መተላለፊያዎችን እና የጋራ መንገዶችን ደህንነት መጨመር እና ማሻሻል።
- በእግር ለሚሄዱ ሰዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ተጨማሪ የመንገድ ማቋረጫዎችን መፍጠር እና አሁን ያሉትን ማሻሻል።
- ሲያትልን ከኩርባ መወጣጫ፣ ተደራሽ ምልክቶች፣ የመኪና ማቆሚያ፣ እና የሕዝብ መጓጓዣ ማቆሚያዎች ጋር የበለጠ ተደራሽ ማድረግ።
- ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ንብረት ባለቤቶችን የሚረዳ የወጪ መጋራት የእግረኛ መንገድ ጥገና ፕሮግራም መዳሰስ።
የሰዎች መንገዶች እና የህዝብ ቦታዎች አካል
መንገዶች ከመዘዋወሪያ ብቻ በላይ ናቸው፣ እነርሱ ደስታ የሚሰጡ እና ዳሰሳ የሚደረጉባቸው ቦታዎችም ጭምር ደግሞ መሆን አለባቸው። የእኛ ራዕይ በጥሩ ሁኔታ የተነደፉ መንገዶች እና የህዝብ ቦታዎች ማህበረሰባችንን ያጠናክራሉ።
ለሰዎች መንገዶች እና ለሕዝብ ቦታዎች ባህሪ የኛ ግቦች:-
- ከተገቢው በታች መዋዕለ ንዋይ የተደረገባቸው አካባቢዎች ላይ በማተኮር፣ ለሰዎች መንገዶች እና ለሕዝብ ቦታዎች ዕቅዶችን ለመፍጠር ከማህበረሰቦች ጋር መስራት።
- ለተሻለ ንፁህ አየር እና ደህንነቱ የተጠበቀ መንገዶች ዝቅተኛ ልቀት ያላቸውን አካባቢዎች ለማዳበር ከማህበረሰቦች ጋር ሽርክና ማድረግ።
- የእግረኛ መንገድ ፍለጋ ፕሮግራማችንን ከማህበረሰብ እና ከክልል አጋሮች ጋር በተለይም በሕዝብ መጓጓዣ ጣቢያዎች ጋ ማስፋፋት።
- በከተማ አቀፍ ደረጃ የዛፍ ሽፋንን ለመጨመር በታሪክ ከተገቢው በታች መዋዕለ ንዋይ የተደረገባቸው አካባቢዎች የዛፍ ተከላ እና የእንክብካቤ ቅድሚያ መስጠት።
የተሽከርካሪ አካል/ ባህሪ
እኛ በተሽከርካሪ ለሚጓዙ ሰዎች እንዲሁም ከሚነዱ ከተሽከርካሪ ውጭ ለሚጓዙ ሰዎች ጋር መንገዱን የሚጋሩትን ሰዎች ደህንነት ማሻሻል እየቀጠልን በእግር የሚሄዱትን፣ ብስክሌት የሚጋልቡትን፣ እና የሚያንከባለሉትን ማበረታታት እንፈልጋለን።
ለተሽከርካሪው ባህሪ/ አካል የኛ ግቦች:-
- ከጥገና ስራው ጎን ለጎን ዘላቂነት ያለው መጓጓዣን የሚያበረታቱ የደህንነት እና ሌሎች ማሻሻያዎችን በማድረግ የከተማ መንገዶችን ዘመናዊ ማድረግ።
- ተሽከርካሪዎች በብቃት እንዲንቀሳቀሱ እና በእግር ለሚሄዱ፣ ብስክሌት ለሚጋልቡ፣ ለሚያንከባልሉ እና የህዝብ ማመላለሻ ለሚጠቀሙ ሰዎች ምቾት እንዲያሻሽሉ መንገዶችን እና የኩርባ ቦታን እንደገና መለወጥ።
- እስከ 2030 የከተማ ተሽከርካሪ ስብስቦችን ወደ 100% ዜሮ ልቀት መቀየር።
- በተፈጥሮ ደህንነቱ የተጠበቀ መንዳትን የሚያበረታቱ እና የሕግ ማስፈጸሚያ ፍላጎትን የሚቀንሱ መንገዶችን መቀየስ/ መንደፍ።
- ለብቻ ሆኖ መንዳትን በመቀነስ፣ የሚጓዙትን የተሽከርካሪ ማይሎች በመቀነስ እና ጤናማ፣ ዘላቂነት ያለው ጉዞ ላይ በማተኮር የመንገድ ፕሮጀክቶችን እንዴት እንደምንገመግም እንደምንችል ማዘመን።
አዲስ እና እየመጣ ያለ ተንቀሳቃሽነት አካል/ ባህሪ
እኛ ጉዞን ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተሻለ ቀላል እና የበለጠ ዘላቂነት ያለው ለማድረግ እንደ የሕዝብ መጓጓዣ በጥያቄ፣ ኢ-ብስክሌቶች፣ የጋራ ቀላል ሞተር ያላቸው ብስክሌቶች እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ያሉ አዳዲስ የጉዞ አማራጮችን እንደግፋለን።
ለአዲሱ እና እየመጣ ላለ ተንቀሳቃሽነት አካል/ ባህሪ የኛ ግቦች:-
- እንደ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሃዊነት እና የአየር ንብረት ምላሽ ያላቸው የማህበረሰብ እሴቶች አዳዲስ የመጓጓዣ ቴክኖሎጂዎች የሚያሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ።
- የጉዞ ፍሰቶችን ለመቆጣጠር፣ ለህዝብ መረጃ ለማቅረብ እና ቀልጣፋ ጉዞን ለማስተዋወቅ ውሂብ መጠቀም።
- ደህንነት መጠበቅ ቅድሚያ በመስጠት ለተገናኙ እና በራስ-ተነጂ ለሆኑ መኪናዎች ፖሊሲዎችን ማደራጀት።
- የኃይል/ የባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን እና ማበረታቻዎችን በማቅረብ ወደ ኤሌክትሪክ የጋራ ተንቀሳቃሽነት እና የጭነት ተሽከርካሪዎች ፈረቃዎችን ማስተዋወቅ።
- በተለይ ከሕዝብ መጓጓዣ ጋር ማገናኘት ሲደረግ የጉዞ ግንኙነቶችን የተሻለ አመቺ ማድረግ።
የኩርባ ዳር (Curbside) አስተዳደር ባህሪ
ኩርባ የተለያዩ አጠቃቀሞች ያሉት የህዝብ ቦታ እንደሆነ እንገነዘባለን። ተወዳዳሪ ፍላጎቶችን ቅድሚያ ለመስጠት እና ለማመጣጠን በአዳዲስ መንገዶች ላይ እየሰራን ነው።
የኛ ለኩርባ ዳር አስተዳደር አካል/ ባህሪ ግቦች:-
- እንደ ተንቀሳቃሽነት፣ ለሰዎች እና ንግዶች ተደራሽነት፣ እና ለመኪና ማቆሚያ የመሳሰሉ አስፈላጊ ተግባራት የኩርባ ድጋፍን እንገነዘባለን።
- በተለያዩ ቦታዎች ውስጥ የትኞቹን ፍላጎቶች እና ጥቅሞች በማስቀደም ለመወሰን መንገዶችን ማደራጀት።
- ዘላቂነት ያለው የጉዞ አማራጮችን እና የሸቀጦችን እና አገልግሎቶችን በግል የመኪና ማከማቻ አቅርቦት ለመደገፍ የኩርባ አጠቃቀሞችን ቅድሚያ መስጠት።
- ዋጋው የሚቀንስ እና አነስተኛ ብክለት የጉዞ አማራጮችን ለማበረታታት የሚከፈልባቸው የመንገድ ላይ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን ማስፋፋት እና ዋጋዎችን መጨመር።
- እንደ ኩርባዎች፣ የመጫኛ ቀጠናዎች፣ እና የብስክሌት/ ባለ ቀላል ሞተር ብስክሌቶች የማቆሚያ ቦታዎች ያሉ ቁሳዊ ንብረቶችን ወቅታዊ መዝገቦች አድርጎ ማቆየት።
ቀጥሎ ምንድነው?
2025 ውስጥ፣ የመጀመሪያውን የትግበራ እቅዳችንን እንፈጥራለን። ይህ እቅድ በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ውስጥ የምንሰራው ስራችን ለጋራ የ STP ራዕያችን እና ግቦቻችን እድገት እንዴት እንደሚያግዝ ያሳያል። እኛ በየአራት ዓመቱ የአፈጻጸም ዕቅዱን እናዘምነዋለን።
STP ክፍል 1
STP ክፍል 2
- STP ክፍል 2 - መግቢያ እና የአውታረ መረብ ውህደት[In English]
- STP ክፍል 2 - የሕዝብ መጓጓዣ አካል[In English]
- STP ክፍል 2 - የጭነት እና የከተማ ሸቀጦች እንቅስቃሴ አካል[In English]
- STP ክፍል 2 - ብስክሌት እና ኢ-ተንቀሳቃሽነት አካል/ ባህሪ[In English]
- STP ክፍል 2 - የእግረኛ ባህሪ/ አካል[In English]
- STP ክፍል 2 - የሰዎች መንገዶች እና የህዝብ ቦታዎች አካል[In English]
- STP ክፍል 2 - የተሽከርካሪ ባህሪ/ አካል[In English]
- STP ክፍል 2 - ኩርባ ዳር (Curbside) አስተዳደር አካል[In English]
- STP ክፍል 2 - አዲስ እና እየመጣ ያለ ተንቀሳቃሽነት አካል[In English]
- STP ክፍል 2 - ሁሉም ክፍሎች ተጣምረው - ተቀባይነት ያገኘ እቅድ ቴክኒካዊ ዘገባ አካላት/ ባሕሪያት[In English] (በትልቅ PDF)