አሁን ይሳፈሩ

አማርኛ • 简体中文 • 繁体字 • 日本語한국어 • Oromiffa • af-Soomaali • Español • Tagalog • ትግርኛ • Tiếng việt • English

የአሁን መሳፈር (Ride Now) ቫውቸሮች ምንድናቸው?

በፈለጉ ጊዜ ተደራሽ፣ በዋጋም ተመጣጣኝ መሳፈርን ያግኙ፣ ምንም ቦታ ማስያዝ አያስፈልግም።

ዕድሜያቸው 65+ የሆኑ ሰዎች፣ አካል ጉዳተኞች እና ተንከባካቢዎች ብቁ ከሆኑ ተሳፋሪዎች ጋር የሚጓዙ ተንከባካቢዎች በወር እስከ 6 የሚደርሱ ነጻ የ$20 ዶላር ቫውቸሮችን፤ ወደ እና ከ እንደ አውቶቡስ ፌርማታዎች እና ሊንክ ቀላል ባቡር፣ ወይም እንደ መናፈሻ ወይም ዘመድ ቤት ጥሩ የመጓጓዣ አገልግሎት ወደሌላቸው ሌሎች በአቅራቢያው ያሉ መዳረሻዎች ያሉ የሕዝብ ማመላለሻ ጣቢያዎች ለየሎው ካብ፣ ኡበር ወይም ሊፍት መሣፈሪያ መጠየቅ ይችላሉ። እነዚህ የ$20 ዶላር ቫውቸሮች እስከ 3 ማይል የሚደርሱ አብዛኛውን ጉዞዎች ሙሉ በሙሉ መሸፈን አለባቸው። ጉዞዎች ሁሉም በሲያትል ከተማ ገደብ ውስጥ መጀመር ወይም ማለቅ አለባቸው።

በከፍተኛ የፍላጎት ጥያቄ ምክንያት የተሳፈሩ አሁን የሙከራ መርሃ ግብር እስከ ሰኔ 2022 ድረስ ተራዝሟል። ብቁ የሆኑ ግለሰቦች በአንድ ተሳታፊ አገልግሎት ለመጠቀም የወረቀት ወይም ዲጂታል ቫውቸሮችን ለመቀበል ሊመርጡ ይችላሉ። እያንዳንዱ የተጠየቀው የቫውቸሮች ስብስብ በየወሩ መጨረሻ (መጋቢት፣ ሚያዝያ፣ ግንቦት እና ሰኔ 2022) ያበቃል፣ እና አዲስ ቫውቸሮች እስከ ሰኔ 3 ቀን 2022 ድረስ ሊጠየቁ ይችላሉ። የመሳፈሪያ ቫውቸሮች ከሰኔ 30 ቀን 2022 በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም። ቫውቸሮች የሚገኙት አቅርቦቶች እስካለ ብቻ ነው።

ስለ ተሳፈሩ አሁን (Ride Now) ፕሮግራም እና ይህ በፍላጎት ጥያቄ ላይ የተመሰረተው ተንቀሳቃሽነት ያለው አገልግሎት እርስዎን ወይም እርስዎ የሚያውቁትን ሰው እንዴት እንደሚረዳ ለበለጠ መረጃ በመረጡት ቋንቋ፣ እባክዎን በ (206) 684-7623 (ROAD) ይደውሉልን ወይም በ RideNow@seattle.gov ላይ ኢሜይል ይላኩልን። የትርጓሜ አገልግሎቶች በነፃ ይገኛሉ።

ለመረጃ በራሪ ወረቀት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።